Mesfin Gutu - Tesfa Adirega paroles de chanson

paroles de chanson Tesfa Adirega - Mesfin Gutu



ክብሬ ጌጤ አንተ ነህ ለእኔ ሽልማቴ
አጠገቤ ሳይህ ወደድኩህ አባቴ
ደጅ አላስጠናኸኝ አንተን ለማግኘት
ሳልፈልግህ መጥተህ ገባህ ከእኔ ቤት
አዝ፦ አንተን ተስፋ አድርጌ
ጌታን ተማምኜ
ኧረ እኔስ ምን አጥቼ (፪x)
ኧረ እኔስ ምን አጥቼ (፬x)
የጠበኩት ሁሉ ያሰብኩት ባይሞላ
አንተ ካለህልኝ ምነው ባይበላ
ተስፋዬ አንተ ነህ የሙጥኝ እላለሁ
ከአንተ ጋራ ኖሮ ሞት ለእኔ ክብር ነው
ትምክቴ ነህ በአንተ እታመናለሁ
የትናንቱን እንዴት ረሳዋለሁ
ተንከባክበህ አሳድገኸኛል
ለነገዬ ምንስ ያስፈራኛል (፪x)
ዓለም ሁሉ ክዶህ ብቻዬን ብቀር
እኔስ አለኝ ለእኔ ሕያው ምስክር
የልጅነቴ አምላክ ከእኔ ጋር ሆነሃል
ጐጆዬ ስትገባ ሙሉ ዓይኔ አይቶሃል
አዝ፦ አንተን ተስፋ አድርጌ
ጌታን ተማምኜ
ኧረ እኔስ ምን አጥቼ (፪x)
ኧረ እኔስ ምን አጥቼ (፬x)
የአጀበ ሲበተን ጐኔ የነበረው
ጊዜና ሁኔታ ወረት ሲቀይረው
አንዱ እንደ ሺህ ሆነ ቤቴን አድምቀሃል
የጐደለኝ የለም ወዳጄ ሆነሃል



Writer(s): Mesfin Gutu


Mesfin Gutu - Negen Ayalehu, Vol. 7
Album Negen Ayalehu, Vol. 7
date de sortie
30-05-2013




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.