Mesfin Gutu - Maranata paroles de chanson

paroles de chanson Maranata - Mesfin Gutu



አስሩ ቆነጃጅቶች ሙሽራውን ሲጠብቁ
አምስቱ ልባሞች ነበሩ
አምስቱ ደግሞ ሰነፎች
ታዲያ አንተ ከየትኛው ነህ
አንቺስ እህቴ ሆይ
ሙሽራው በደጅ ነው
ለኩስ ኩራዝህን ለኩሽ ኩራዝሽን
አዝ፦ ማራናታ አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ (፫x)
ናፍቆታችን አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ
ማራናታ (ቶሎ ና) አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ
የዚህ ዓለም መከራ እጅግ ቢበረታ
ሙሽራው በደጅ ነው ሊመጣ
እስኪ እንበል ማራናታ
አዝ፦ ማራናታ አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ
ማራናታ አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ
ሙሽራ ሆይ ቶሎ ቶሎ
ሙሽራ ሆይ ቶሎ (፬x)
እረፍት የተጠራ እንደኛ ማነው
በምድር ተቀምጦ በሠማይ ርስት ያለው (ርስት ያለው (፪x))
እንሄዳለን አዲሲቱ ሃገር (ሃገር ሃገር ሃገር አለኝ)
አገር አለኝ በሠማይ (በሠማይ)
ከበጉ ጋር በደስታ ልንኖር (ልንኖር)
ሙሽራው ሊመጣ በደጅ ነው (በደጅ ነው (፪x))
በደጅ ነው በደጅ ነው (በደጅ ነው)
አዝ፦ ማራናታ (ቶሎ ቶሎ ና)
አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ (፬x)



Writer(s): Mesfin Gutu


Mesfin Gutu - Negen Ayalehu, Vol. 7
Album Negen Ayalehu, Vol. 7
date de sortie
30-05-2013




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.