Текст песни




እንዲያው በሰው ወግ ብቻ
ባሉኝ ሚዛን በፍርጃ
በራስ ህግ በአይን እይታ
አያጥፍ የልቤን ደስታ
በፍቅር ሕግ አምላክ በንፁህ ቅን ጨዋታ
ፍፁም በዘፈን ድምፅ የለም ከልካይ ጌታ
ክፉ ግን ክልክል ነው እርሱማ መቼ ጠፋን
በቃል ቢሆን በዜማ መዝሙር አሉትም ዘፈን
እልልታማ ንፁኋ ሆታ
በረከት ነች ለሰው ልጅ ደስታ
በፍቅር ሕግ አምላክ በንፁህ ቅን ጨዋታ
ፍፁም በዘፈን ድምፅ የለም ከልካይ ጌታ
እምቢልታ ነው ዘፈን መካሻ
የእንባ ካሳ የሀዘን ማስረሻ
በፍቅር ሕግ አምላክ በንፁህ ቅን ጨዋታ
ፍፁም በዘፈን ድምፅ የለም ከልካይ ጌታ
በዚያ ቆነጃጅት በመዝሙር ሲዘፍኑ
ተሸርበው እንጂ መች ጠጉር ሸፈኑ
በዚያ ደግሞ ወንዶች የእኛን ዜማ ሰድበው
ወግ ጥሰው የለም ወይ ራስ ተከናንበው
እንዲያው በሰው ወግ ብቻ
ባሉኝ ሚዛን በፍርጃ
በእንዲያው በሰው ወግ ብቻ
አያጥፍ የልቤን ደስታ
በፍቅር ሕግ አምላክ በንፁህ ቅን ጨዋታ
ፍፁም በዘፈን ድምፅ የለም ከልካይ ጌታ
ክፉ ግን ክልክል ነው እርሱማ መቼ ጠፋን
በቃል ቢሆን በዜማ መዝሙር አሉትም ዘፈን
የሙሽራ የሰርግ እምቢልታ
ቅን ነው ዘፈን የዜማ ደስታ
በፍቅር ሕግ አምላክ በንፁህ ቅን ጨዋታ
ፍፁም በዘፈን ድምፅ የለም ከልካይ ጌታ
ቀድሞ ባለ ነው ወይ የኛ የኛ መዝሙር
በአዝማሪ አሳበው አዚመዋል ለምስል
በመዝሙር ዘፈኑ በዘፈን አዘመርን
ተረፍን እንጂ መቼም ተራፊም አከበርን
በዛ ቆነጃጅት በመዝሙር ሲዘፍኑ
ተሸርበው እንጂ መች ጸጉር ሸፈኑ
ከዛ ደግሞ ወንዶች የኛን ዜማ ሰድበው
ወግ ጥሰው የለም ወይ ራስ ተከናንበው
በፍቅር ሕግ አምላክ በንፁህ ቅን ጨዋታ
ፍፁም በዘፈን ድምፅ የለም ከልካይ ጌታ
ክፉ ግን ክልክል ነው እርሱማ መቼ ጠፋን
በቃል ቢሆን በዜማ መዝሙር አሉትም ዘፈን





Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.
Загрузка
Загрузка