Текст песни




አልፎ ባበቃ እርሙን በተዘጋ
እንዲያ ነበርሽ ቋንቋ ክስ የለም ዛሬጋ
ህይወት ዳግም ተነስታ
ከልጅነት ነቅታ
ክፉውን ጠልታና ንቃ
እያለች ልብ አውቃ
አልፎ ባበቃ እርሙን በተዘጋ
እንዲያ ነበርሽ ቋንቋ ክስ የለም ዛሬጋ
ፍቅርን በእውነት ተጠምታ
ቅኑን መንገድ መርጣ
ክፉውን ንቃና ርቃ
ከዳነች ልብ አውቃ
ለበጎ አይባል ነገር ምኑም ክፉ ነገር
ባላወኩት በነበር ጭንቁን ሳላይ ቢቀር
ከእሳት ከሚንቦገበግ
ሆንኩ ወጣሁ እንደ ትንታግ
በምክር በሚታደግ
ታዞ ተሰምቶ በሚደረግ
የሚመለጥ ተተርፎ
በጥቅም ብቻ ከመጥፎ
በቅን መንገድ ነው መውጫው
ሰው ካለበት ማምለጫው
አልፎ ባበቃ እርሙን በተዘጋ
እንዲያ ነበርሽ ቋንቋ ክስ የለም ዛሬጋ
ህይወት ዳግም ተነስታ
ከልጅነት ነቅታ
ክፉውን ጠልታና ንቃ
እያለች ልብ አውቃ
አጥፍቶማ ተኝቶ ከንቱ ቢከራርም
ምንም የለም ለበጎ ክፉ ሳይታረም
ቀልጦ መቅረትም አለ
በጎ በከንቱ የት አለ
በመልካም ነው የሚመለጥ
ሰክኖ ተደርጎ በሚገለጥ
የሚመለጥ ተተርፎ
በጥቅም ብቻ ከመጥፎ
በቅን መንገድ ነው መውጫው
ሰው ካለበት ማምለጫው
ፍቅርን በእውነት ተጠምታ
ቅኑን መንገድ መርጣ
ክፉውን ንቃና ርቃ
ከዳነች ልብ አውቃ
ህይወት ዳግም ተነስታ
ከልጅነት ነቅታ
ክፉውን ጠልታና ንቃ
እያለች ልብ አውቃ
ህይወት ዳግም ተነስታ
ከልጅነት ነቅታ
ክፉውን ጠልታና ንቃ





Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.
Загрузка
Загрузка