Текст песни




ፊት በውሀ ላይ እንደሚታይ ያህል ቢሆንም
የሰው ልብ እኮ ለሰውም ይታያል
የሰው ፊት ውስጡን ያሳብቃል
ድምፁም
ደሞ ሰው ውስጡ ውብ ሲሆን
እውነተኛ ውበት
ከድብቅነት እያለፈ እወጣ እወጣ ሲመጣ
ላይን አምሮ አለመታየት ያለመቻል ሚስጥር
እጅግ ይገርማል
በመልካም እንደ ልቡ ምርጫ
ላይ ታቹን የምድሩን ዳርቻ
ነው ብሎ ሰራው ቅን በጎ
ሁሉን በጊዜው ውብ አርጎ
ነው ብሎ ሰራው ቅን በጎ
ሁሉን በጊዜው ውብ አርጎ
እኛ ነን እና
ውብ የእጆቹ ስራ
ሁላችን ነን እና
ድንቅ የእጆቹ ስራ
በመልካም እንደ ልቡ ምርጫ
ላይ ታቹን የምድሩን ዳርቻ
ነው ብሎ ሰራው ቅን በጎ
ሁሉን በጊዜው ውብ አርጎ
እኛ ነን እና
ውብ የእጆቹ ስራ
ሁላችን ነን እና
ድንቅ የእጆቹ ስራ
አያልቅም ትርፏ
ሰፊ ነች ምድሯ
ለእያንዳንዳችን
አርጓት ድርሻችን
እኛ ነን እና
ውብ የእጆቹ ስራ
ሁላችን ነን እና
ድንቅ የእጆቹ ስራ
ልቡን ሲያጠራ
ውስጡን ሲያበራ
ሰው ሁሌም ውብ ነው
ድንቁ ውብ ስራ
ለእድሜው በከንቱ ባይሰጋ
ሰው ክብር አለው ዋጋ
ለኔ ሁሌም ሰው ሲፈጠር
ውብ ቢነጣ ቢጠቁር
ውብ የእጆቹ ስራ
ሁላችን ነን እና
ድንቅ የእጆቹ ስራ
እኛ ነን እና
ውብ የእጆቹ ስራ
ሁላችን ነን እና
ድንቅ የእጆቹ ስራ





Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.
Загрузка
Загрузка