Текст песни




ምን እንድልልህ ነው ፍቅሬ እንዲ ናት ብለህ
እንደሷ ሳልቀርብህ ያማህልኝ ምለህ
ካንተው ሰምቼ ካንተው ብጓደን
ሳላውቃት በጭፍን ብፈርድ
ታየኛለህ ወይ እኔስ ብፈቅድ
ከሷ አልሻል እንዲያስ ብነጉድ
ካፏ አልሰማው አላውቅ የሷን
ቅንም ቢሆን ባይሆን መልሷን
በነበር ፍቅረኛዋ
በልብ ሚስጥረኛዋ
ወይ የሚታማ ሰው በክፉ የሚነሳ
ኖሮ ባየ ክሱን
ባወቅንለት መልሱን
ካንተው ከቆየች ከምታውቃቷ
እንዲሁም ካዲሲቷ
ልትቆጥረኝ ነው ወይ እንደምሻል
ልትል እኔን ይገባሻል
ባፈቀራት አፍ በሳማት
አይከብድም ወይ ለሩቅ ማማት
በቅርብ አማካሪዋ
በነበር አፍቃሪዋ
ወይ የሚታማ ሰው በክፉ የሚነሳ
ኖሮ ባየ ክሱን
ባወቅንለት መልሱን
ምን እንድልልህ ነው ፍቅሬ እንዲ ናት ብለህ
ከሷ ላልቀረብኩህ የምታማት ምለህ





Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.
Загрузка
Загрузка