Gossaye Tesfaye - Tameryalesh текст песни

Текст песни Tameryalesh - Gossaye Tesfaye



ሰው በቃህ እስኪለኝ ተመክሬ ተመክሬ
ችዬ እንዴት ልሰማ የሰው ወሬ የሰው ወሬ
ትቼ እንዳልተዋት ልቤ በሷ ታሞ
ታምራለች ደ′ሞ
ልሰጣት አይደልወይ ንፁህ ልቤን ንፁህ ልቤን
እሷ መች ተገኝታ ወስዳ ቀልቤን ወስዳ ቀልቤን
ትቼ እንዳልተዋት ልቤ በሷ ታሞ
ታምራለች ደ'ሞ
ደግሞ
ገና ከማለፍሽ ቀልብ የራቀኝ እኔ
አንቺ ምን ታደርጊው ወዶ ያኮራሽ አይኔ
ዘነጋሁኝ ብለሽ ተመላለሺና
ደግሞ ይደንግጥ ልቤ ደግመሽ እለፊና
ላሳውቃት እንጂ እስክትገባ ከእጄ
ጉዳይ ባደርገው ማለፏን በደጄ
ደሞ በዚ ጊዜ ምን ሚታይ አለና
ከሷ ወዲያ ላሳር አምላክ አይኔን ጤና
ታምሪያለሽ ታምሪያለሽ
በልቤ ቦታ አለሽ
እስኪያመኝ አምረሻል
ከልቤ ገብተሻል
ታምሪያለሽ ታምሪያለሽ
በልቤ ቦታ አለሽ
እስኪያመኝ አምረሻል
ከልቤ ገብተሻል
ሰው በቃህ እስኪለኝ ተመክሬ ተመክሬ
ችዬ እንዴት ልሰማ የሰው ወሬ የሰው ወሬ
ትቼ እንዳልተዋት ልቤ በሷ ታሞ
ታምራለች ደ′ሞ
ልሰጣት አይደልወይ ንፁህ ለቤን ንፁህ ልቤን
እሷ መች ተገኝታ ወስዳ ቀልቤን ወስዳ ቀልቤን
ትቼ እንዳልተዋት ልቤ በሷ ታሞ
ታምራለች ደ'ሞ
ደግሞ
አንቺን ለመውደዴ ባልሆን እውነተኛ
ምን አስቀምጦ አዋለኝ እንደ በሽተኛ
ሰው ይማርህ ብሎ ደፍሮም ባይጠይቀኝ
አውቆታል ህመሜን ባንቺ እንደጨነቀኝ
ላሳውቃት እንጂ እስክትገባ ከእጄ
ጉዳይ ባደርገው ማለፏን በደጄ
ደሞ በዚ ጊዜ ምን ሚታይ አለና
ከሷ ወዲያ ላሳር አምላክ አይኔን ጤና
ታምሪያለሽ ታምሪያለሽ
በልቤ ቦታ አለሽ
እስኪያመኝ አምረሻል
ከልቤ ገብተሻል
ታምሪያለሽ ታምሪያለሽ
በልቤ ቦታ አለሽ
እስኪያመኝ አምረሻል
ከልቤ ገብተሻል
ታምሪያለሽ ታምሪያለሽ
በልቤ ቦታ አለሽ
እስኪያመኝ አምረሻል
ከልቤ ገብተሻል



Авторы: Gossaye Tesfaye


Gossaye Tesfaye - Satamagne Bela
Альбом Satamagne Bela
дата релиза
01-12-2010




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.