Teddy Afro - Abugida (Live) Lyrics

Lyrics Abugida (Live) - Teddy Afro



ሀ-ግዕዝ ሁ-ካልዕ ሂ-ሳልስ ሃ-ራብዕ ሄ-ሃምስ ሆ-ሳብእ
ሀ-ግዕዝ ሁ-ካልዕ ሂ-ሳልስ ሃ-ራብዕ ሄ-ሃምስ ሆ-ሳብእ
የወደድኳት በማለዳ
በልጅነት በአቡጊዳ
የፍቅር ቃል መቁጠሪያዬ
የመጀመሪያዬ
አቡጊዳ
የኔታ ለመምህሩ
አቡጊዳን ሲያስተምሩ
ማልዳ ወግታኝ ከፊደል ጣት
አሁን ከየት ላምጣት
አቡጊዳ (አቡጊዳ)
አቡጊዳሄውዞ አቡጊዳ
አቡጊዳ ኦዳ
ሁሌ የጀማሪ እዳ
አቡጊዳሄውዞ አቡጊዳ
አቡጊዳ ኦዳ
ሁሌ የጀማሪ እዳ
ምሎላታል በፊደሉ
ላይታጠፍ ልቤ ቃሉ
ይኑር እንጂ ሲከልሳት
'ሀ' እንዴት ሊረሳት
አቡጊዳ
ገና ልጅ ነኝ ብላቴና
ስለፍቅር መች አውቅና
አስጠናችው ልቤን ወስዳ
የፍቅር አቡጊዳ
አቡጊዳ (አቡጊዳ)
አቡጊዳሄውዞ አቡጊዳ
አቡጊዳ ኦዳ
ሁሌ የጀማሪ እዳ
ሀ-ግዕዝ ሁ-ካልዕ ሂ-ሳልስ ሃ-ራብዕ ሄ-ሃምስ ህ-ሳድስ ሆ-ሳብእ
መልዕክተ ዮሐንስ ሐዋርያ ወልደዘብድዮስ
ንዜንወክሙ በእንተ ውዕቱ
መልዕክተ ዮሐንስ
የወደድኳት በማለዳ
በልጅነት በአቡጊዳ
የፍቅር ቃል መቁጠሪያዬ
የመጀመሪያዬ
አቡጊዳ
የኔታ ለመምህሩ
አቡጊዳን ሲያስተምሩ
ማልዳ ወግታኝ ከፊደል ጣት
አሁን ከየት ላምጣት
አቡጊዳ
ሀ-ግዕዝ ሁ-ካልዕ ሂ-ሳልስ ሃ-ራብእ ሄ-ሃምስ ህ-ሳድስ ሆ-ሳብእ
ሀ-ግዕዝ



Writer(s): Teddy Afro


Teddy Afro - Yasteseryal Live (World Tour Edition)
Album Yasteseryal Live (World Tour Edition)
date of release
01-07-2005




Attention! Feel free to leave feedback.