Teddy Afro - Hewan Endewaza (Live) Lyrics

Lyrics Hewan Endewaza (Live) - Teddy Afro



ልቤም ተደላደለ ጎኔም ደላው መሰለኝ
አንችን ስለመውደዴ አገር ሰምቶ ጉድ ቢለኝ
ከወደድኩሽ ወዲያ ምንድንነው
ቢጠፋም ስሜ ነው
ልቤም ተደላለ ጎኔም ደላው መሰለኝ
አንችን ስለመውደዴ አገር ሰምቶ ጉድ ቢለኝ
ከወደድኩሽ ወዲያ ምንድንነው
ቢጠፋም ስሜ ነው
በዚች አለም ስኖር ሰው ነበር ረሀቤ
ምኞቴ ተሳካ ባንቺ አረፈ ልቤ
ወሬ ቢጓዝ በቀን በሌሊት ጨረቃ
አንች አለሽኝ ለኔ ስም አልፈራም በቃ
ካበጀሽ ፈጣሪ ከኔ ወስዶ ለኔ
እንዴት እኖራለሁ ያለግራ ጎኔ
ሄዋን እንደዋዛ ፍሬዋን በልተሽ
በኔና በምድር ሞት እንዳመጣሽ
ለባከነው ልቤ ራርቶ ልብሽ
መጽናኛ ሆኖኛል ክሶኛል ፍቅርሽ
ፍቅራችን ይወሰን ይሁን አቻ ለአቻ
እኔም አንችን ብየ አንችም እኔን ብቻ
ተረታና ልኔ ለፍቅር ለፍቅር ተገዛ
በሆዴ ቤት ሰራችሄዋን እንደዋዛ
ሄ------ሄዋን እንደዋዛ
ሄ------ሄዋን እንደዋዛ
እንደዋዛ
ሄ------ሄዋን እንደዋዛ
እንደዋዛ
ሄ------ሄዋን እንደዋዛ
ልቤም ተደላለ ጎኔም ደላው መሰለኝ
አንችን ስለመውደዴ አገር ሰምቶ ጉድ ቢለኝ
ከወደድኩሽ ወዲያ ምንድንነው
ቢጠፋም ስሜ ነው
ልቤም ተደላለ ጎኔም ደላው መሰለኝ
አንችን ስለመውደዴ አገር ሰምቶ ጉድ ቢለኝ
ከወደድኩሽ ወዲያ ምንድንነው
ቢጠፋም ስሜ ነው
ሲባክን አንጀቴ የሀሳብ ስንቅ ይዞ
አበቃልኝ ዛሬ የብቻየ ጉዞ
ልቤ ባንች ነቅቶ ከተደላደለ
ስሜ ቢዞር ባገር ቢጠፋስ ምን አለ
ካበጀሽ ፈጣር ከኔ ወስዶ ለኔ
እንዴት እኖራለሁ ያለግራ ጎኔ
ሄዋን እንደዋዛ ፍሬዋን በልተሽ
በኔና ለምድር ሞት እንዳመጣሽ
ለባከነው ልቤ እራርቶ ልብሽ
መጽናኛ ሆኖኛል ክሶኛል ፍቅርሽ
ፍቅራችን ይወሰን ይሁን አቻለአቻ
እኔም አንችን ብየ አንችም እኔን ብቻ
ተረታና ልቤ ለፍቅር ተገዛ
በሆዴ ቤት ሰራሽ ሄዋን እንደዋዛ
ሄ------ሄዋን እንደዋዛ
ሄ------ሄዋን እንደዋዛ
እንደዋዛ
ሄ------ዋን እንደዋዛ



Writer(s): Teddy Afro


Teddy Afro - Yasteseryal Live (World Tour Edition)
Album Yasteseryal Live (World Tour Edition)
date of release
01-07-2005




Attention! Feel free to leave feedback.