Mesfin Gutu - Mene Elalehu текст песни

Текст песни Mene Elalehu - Mesfin Gutu




እንደ ሲና ምድር እንደ በረሃዉ
ጠል ከእርሱ እርቆ ፡. (1) .
ትካዜ ሰፍኖበት ሆኖ ረዳት አልባ
እንዲህ ያለው ምስኪን ልምላሜን ሰማ
አሄ ልምላሜን ሰማ
አዝ፦ ምን እልሃለው (፫x)
ከእግርህ ሥር ወድቄ አመሰግናለው (፪x)
ብቸኝነት ዓለም ወግ ሆኖ በሕይወቴ
አጠገቤ ነበር ለካስ ደጉ አባቴ
ቅርበቱን አወኩት ድምጹንም ሰማሁት
እንደ ብዙ ወዳጅ ሆኖ አገኘሁት
አሄ ሆኖ አገኘሁት
ያንን የጭንቅ ቀን የብቸኝነቴን
ክንድህ ባይረዳኝ ፀጋህ ባያግዘኝ
ኧረ እኔስ የት ነበርኩኝ (፪x)
እናት አባት ዘመድ ለእኔስ ኢየሱሴ ነው
ቀን ከሌት ስራመድ ልቤ የሚያስበው
በኛ ክፉ ቀናት ረዳት በሌላቸው
መጽናናት ሆነልኝ ዳስሼው ነክቼው
አሄ ዳስሼው ነክቼው
አዝ፦ ምን እልሃለው (፫x)
ከእግርህ ሥር ወድቄ አመሰግናለው



Авторы: Mesfin Gutu



Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.
//}