Mesfin Gutu - Yalayehut Alem текст песни

Текст песни Yalayehut Alem - Mesfin Gutu



የተደረገልኝን አይቼ
ከአንተ የተቀበልኩትን አይቼ
በፊትህ ቅኔን ተቀኘሁኝ
እንዲህ አልኩኝ
አንተ ጌታዬ ነህ አንተ
ኧረ አንተ ንጉሤ ነህ አንተ
አንተ ጌታዬ ነህ አንተ
ኧረ አንተ አባቴ ነህ አንተ
ያላየሁት ዓለም ያልቀመስኩት ኑሮ
በጌታ ሆነልኝ ይገርማል ዘንድሮ
ተመስገን ነው እንጂ ሌላ ምን ይባላል
የአምላኬ ቅናት ይህንን አድርጓል
ተመስገን ነው እንጂ ሌላ ምን ይባላል
የአምላኬ ቅናት ይህንን አድርጓል (፪x)
እንዲህ ነው ጌታ ሲረዳ
እንዲህ ነው ኢየሱስ ሲያሳርፍ
(እንዲህ ነው ጌታ ሲረዳ
እንዲህ ነው ኢየሱስ ሲያሳርፍ) (፪x)
ደግሜ ደግሜ ጌታን አመልካለሁ
ጌታን አከብራለሁ (፪x)
እርሱ የእኔ አባት መድሃኒቴ ነው (፫x)
አቅም ብርቱ ሳለ ጉልበቴ ሳይደክም
ለዚህ ከንቱ ዓለም ልቤን አላዝልም
አቅም ብርቱ ሳለ ጉልበቴ ሳይደክም
ለዚህ ከንቱ ዓለም ልቤን አላዝልም (፪x)
እንደምን ይቻላል ያለ ጌታ ሆኖ
በራስ መተማመን ድጋፍ ተሸፍኖ
ዓለምን ናቅ አድርጐ ጌታን መወዳጀት
ይህ ታላቅ ጥበብ ነው የሠማይ በረከት
ዓለምን ናቅ አድርጐ ጌታን መወዳጀት
ይህ ታላቅ ጥበብ ነው የሠማይ በረከት (፪x)
እንዲህ ነው ጌታ ሲረዳ
እንዲህ ነው ኢየሱስ ሲያሳርፍ
(እንዲህ ነው ጌታ ሲረዳ
እንዲህ ነው ኢየሱስ ሲያሳርፍ) (፫x)



Авторы: Mesfin Gutu


Mesfin Gutu - Negen Ayalehu, Vol. 7
Альбом Negen Ayalehu, Vol. 7
дата релиза
30-05-2013




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.