Mesfin Gutu - Hatyate Tesereye текст песни

Текст песни Hatyate Tesereye - Mesfin Gutu



ኢየሱስ ስለእኛ መስቀል ተሸክሞ
ቀራንዮ መንገድ ላይ በጅራፍ ተገርፎ
ጐልጐታ መስቀል ላይ በግፍ ተሰቀለ
እንደጅራት ደሙ በሜዳ ፈሰሰ
ሞተ ተቀበረ ተስፋ የለው ብለው
ተከታይ ልጆቹ በሃዘን ተመተው
አዳኛችን ኢየሱስ በክብር ተነሳ
ከሙታን አለት ውስጥ እኛንም አስነሳን
በትንሳኤው ኃይል ማሸነፍ ያገኙ
ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገሩ
የከበረ ሠማይ ይጠብቃቸዋል
በ. (1) .ቸው ሁሌ በእዚያ ይሆናል
ኃጢአት ተወገደ በጌታችን ደም
በደል ተሰረየ በመሲሁ ደም
የዘላለም ጥፋት አይታሰብም
ክቡር ለእርሱ ይሁን ለመድሃኒዓለም
የዘላለም ጥፋት አያገኘንም
ክቡር ለእርሱ ይሁን ለመድኃኒዓለም
ኃጢአት ተወገደ በመሲሁ ደም
በደል ተሰረየ በጌታችን ደም
የዘላለም ጥፋት አይታሰብም
ክቡር ለእርሱ ይሁን ለመድሃኒዓለም (፪x)
አማኑኤል ከእኛ ጋር ነው (፬x)
መዳናችን በእርሱ ነው (፫x)
አማኑኤል ከእኛ ጋር ነው (፬x)
መዳናችን በእርሱ ነው (፫x)



Авторы: Mesfin Gutu


Mesfin Gutu - Negen Ayalehu, Vol. 7
Альбом Negen Ayalehu, Vol. 7
дата релиза
30-05-2013




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.