Текст песни




አንደኛው የዘመን ሰዉ
የመቶ ዐመት ታላቅ ኋለኛው
ባዶ እግሩን ሀገሩን ያቀና
በላብ በደሙ የመሬቱን ድንበር የሳለው
አምላኩ ፍቃድ የሚኖረው በፆም በፀሎቱ ሠማይን የሚቀደው
ጠና ይስጥልኝ ይላል ወዳጁን ሲያገኘው
መልካሙን ብቻ ነው የሚመኘው
የሰው ስሜትን ነዉ የለበሰው
ደሙ ትኩስ ለጠላቱ ሀገር ይጨሳል ሲቆጣ ስሜቱ
ዐይኑ ፈጦ አፍሮ ፀጉሩ አንበሳን መስሎ ከነምንሽሩ
ውስጡ ደሞ አለ ትህትና ዛሬን የሚያስንቅ ዛሬን የሚያስቀና
ቤትማ የእግዜር ነው ብሎ መኝታ ለቆ ከመደብ ያድራል መሬት ወድቆ
የሰው ልክ የሰው መልካም ስብእናው አይለካም
አሱን መስሎ እራሱን ቀርፆ ባህሪውን ስሎ
ከወገኑ ከሚወደው እንደ ወጉ እንደ ቀዬው
ሳይማረጥ ዘር ሳይቆጥር ኖሮ ተቻችሎ
የአባት አባት የሀገር አድባር የአዛውንቱ ፍቅራቸውን ምርቃቱን በረከቱን ምክሩን ተቀብሎ
ፈጣሪውን አከበረ በሰው ልጅ ላይ የቆጠረ የሠማዩ በምድር ላይ ሊፈታ ሰው በአምላኩ ብሎ
ግን ዛሬ በህይወት የለም ከአፈር በታች ውሎ
የሶስት ዘመን ሰው ቅድመ አያት እኔ የልጅ ልጅ
ሁለተኛው እኔ ነኝ የዚ ዘመን ነኝ
ከአንደኛው የተመዘዝኩት
ግን ተለወጥኩ መልሼ እራሱን የምወቅሰው
ታሪኩን የማራክሰው
ኋላ ቀር ነህ እለዋለሁ
ምን ተውክልኝ እለዋለሁ
ሰዉነቱን አረክሳለሁ
የሰራውን አፈርሳለሁ
ከአፈሩ በታች ገብቼ
ሰላም አረፍቱን ነስቼ
በነገር ቢላ ስጠቀጥቀው
እሱ ግን አያወጋኝም ሄድዋል
መልስም የለው
እሱ ግን መልስም የለው
ከወንድሜ ጋር ሰላም የለኝም
መንገዴ ሁሉ የጠፋብኝን
Technology የበዛብኝ
በቸኝነት የሚያጠቃኝ
ትልቅ ሀገረ ተረክቤ ትንሽ ሆኜ ጠቦ ሃሳቤ
ከፋፍዬ አሳነስኳት መላወሻም አሳጣኋት
የኔ ስልጣኔ ሆነ መጥኔ
የሶስት ዘመን ሰው ቅድመ አያት እኔ የልጅ ልጅ
የሶስተኛ ዘመንን ሰው ፈራሁት
ከኔ ይብሳል እሱን ፈራሁት
ታሪኬን ሁሉ እየበረበረ
የተፃፈውን እየመነዘረ
ሀገር እንደቀማሁት ሲያዉቅ ደነገጠ
ንዴቱ ሁሉ ምድርን አግሎ አቀለጠ
በጣም ጭሶ እርር ብሎ እሳት እያናፋ
ገላ አጥነትን የሚሰብር ቃላት እየተፋ
ከምድር በታች ወድቄ አፈር ቢጫነኝም
ያረኩትን አውቃለሁ እና እረፍትስ የለኝም
ሀገር የለው ወገን የለው ከሜዳ በትኜ
አረኩት ሆደ ባሻ ታሪኩን አጥፍቼ
ከኔ የባሰ አውሬነቱ ከውስጡ ቢወጣም
ጥፋቱም አይመዘን ሀዘኑ ቅጥ አጣ





Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.
Загрузка
Загрузка